በጃፓን ውስጥ ያለው የስደተኞች ተስፋ መቁረጥ


 

ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ)

<

 

 

 በጃፓን ውስጥ ያለው የስደተኞች  ተስፋ መቁረጥ እየጨመረ ሄዷል።

በኡሺኩ ኢባራኪ በሚገኘው የምስራቅ ጃፓን የኢሚግሬሽን ማእከል ከሚገኙት በግምት 100 የሚጠጉ እስረኞች  መካከል በግንቦት 10 በጀመረው የረሃብ አድማ በይበልጥ እየጨመረ በመሄድ ላይ  ነው  የሚገኘው ። አድማ  መቺዎቹ ስደተኞች  ረጅም የእስር ጊዜ እንዲያበቃ እየጠየቁ ነው የሚገኙት።በአሁን ወቅት በተለይም ከአንድ አመት በላይና ከዚያም በላይ ቆይተው  በተፈቱ እስረኞች ሕይወት ላይም ከባድና ተግባራዊ ሊሆኑ የማይችሉ ገደቦችን የሚያስቀምጥ ጊዜያዊ የመልቀቂያ  ወረቀት የተሰጣቸው  ሲሆን መዝናናትም ሆነ ከአካባቢያቸው  መራቅ አይፈቀድላቸው።  በእስር ቤት ውስጥ  ያለው መገለልም  በየጊዜው  እየጨመረ ነው።የመረጃ  እጦትና በህክምና በኩልም ቸልተኝነት ብዙ ጊዜ ይታያል። የረዥም ጊዜ እስረኞች በአካልና በአእምሮ በሽታና በጤና መታወክ አብዛኛዎቹ ስደተኞች  የሚሰቃዩ በመሆናቸው ይህ ደግሞ የእስረኞች ቁጣ  እንዲባባስ  አድርጎታል

 

 

በጃፓን የማቆያ ማእከላት የሚገኙ ስደተኞች የረሃብ አድማዎች የሚያደርጉ ሲሆን በዚሁ የረሃብ አድማ ምክንያት አንዳንዴም አሳዛኝ መዘዞችን እየሳቡ  ይገኛሉ።  ሰኔ 24 ቀን አንድ ናይጄሪያዊ ሰው በናጋሳኪ ግዛት በሚገኘው ኦሙራ ማቆያ ማእከል ባደረገው የረሃብ አድማ ምክንያት ህይወቱ አለፏል።  በምስራቅ ጃፓን የኢሚግሬሽን ማእከል እየተካሄደ ያለው የረሃብ አድማ በኡሺኩ ኖ ካይ የውጭ እስረኞችን ወክሎ  የሚደግፈውና የሚከራከረው መንግሥታዊ ያልሆነው  ድርጅት ሁኔታውን  በአሁኑ ወቅት እየተከታተለው  ነው የሚገኘው።  የኡሺኩ ኖ ካይ መሪ የሆኑት ኪሚኮ ታናካ፣ የኢሚግሬሽን ቢሮ የረሃብ አድማቸውን እንዲያቆምላቸው ለተስማሙ  እስረኞች ለበርካታ ሳምንታት ጊዜያዊ መልቀቅ ወረቀትን በመስጠትና  በማፅደቅ ሁኔታውን ለመቆጣጠር በሚሞክርበት ጊዜ የስራ ማቆም አድማ የሚያደርጉ እስረኞች ቁጥር  በየጊዜው  እንደሚዋዥቅ ያስረዳሉ።  ነገር ግን ከሁለት ሳምንት በኋላ እንደገና እነዚሁ በጊዛዊ ወረቀት የተለቀቁ ስደተኛ የሆኑ እስረኞች ተመልሰው  ታስረዋል። '' እንደዚህ አይነት ሁኔታ  ያጋጠማቸው ሰዎች፣ በሐቀኝነት ላይ በተመረኮዘ  መልኩ  በሁኔታው በሚያስደንቅ ሁኔታ በማዘን ተቆጥተዋል።''  በማለት ታናካ ይገልጻሉ

 

 በምስራቅ ጃፓን  የሚገኙ 

የኢሚግሬሽን ማእከል ታሳሪዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑ ስደተኞች ናቸው።  አብዛኛዎቹ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወይም ከቪዛቸው በላይ የቆዩ ናቸውአብዛኛዎቹ ከደቡብ ምስራቅ እስያ፣ አፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ የመጡ ናቸው።  በ2018 እ. ኤ.አ ጃፓን ከ10,493 የስደተኛ ማመልከቻዎች ውስጥ 42ቱን ብቻ ተቀብላለች።  እነዚህን ዕድሎች ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ብዙ አመልካቾች በሶስተኛ ሀገር ጥገኝነት የመጠየቅ እድልን ለመሞከር ይፈልጋሉ። ነገር ግን ጥቂት ሀገራት እንደ ጃፓን ባለ ሀብታም ሀገር ስደተኞችን ለመውሰድ ፈቃደኛ አይመስሉም።  በተግባር ለታሳሪዎች ብቸኛ መውጫው ወደ አገራቸው መመለስ ነው።  ነገር ግን ብዙዎች በአገራቸው የሚደርስባቸውን ችግር በመፍራት በጃፓን ይቆያሉ ለረጅም ጊዜ በእስር ጊዜ የሚቆዩ ስደተኞች በርካታ ናቸው።አብዛኛዎች በተደጋጋሚ እየታሰሩ  በጊዜያዊ  ወረቀት ይለቀቁና ትንሽ  ቆይተው  ደግሞ  ዳግመኛ እስር ቤት ይከቷቸዋልይህን የእስር  ሁኔታን ስደተኞቹ የተለማመዱት ይመስላል።

 

 በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ኡሺኩ ኖ ካይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የስደተኞች ሰራተኞች ኮሚቴ ለቀረበላቸው መጠይቅ ምላሽ ለመስጠት በጃፓን የሚገኙ የእስር ቤቶችን ዘገባ አጠናቅረው  ነበር።  የሪፖርቱ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት በኡሺኩ ኖ ካይ አባላት ወደ ምስራቅ ጃፓን የኢሚግሬሽን ማእከል አዘውትረው እስረኞችን ይጎበኙ እንደነበርና በ2018 በተደረገ የመረጃ አሰባሰብ 265 እስረኞች ላይ ጥናት አድርገው  ነበር

 

እንደ ዘገባው ከሆነ የረዥም ጊዜ እስር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለመደ መጥቷል።  የዳሰሳ ጥናት ምላሽ ሰጭዎች 77 በመቶ የሚሆኑት ከአንድ አመት በላይ ሲታሰሩ 36 በመቶ የሚሆኑት ከሁለት አመት በላይ ታስረዋል።  ዋስ ያላቸው እስረኞች በአማካይ ከ1,000 እስከ 2,000 ዶላር የተቀማጭ ገንዘብ ለጊዜያዊ መልቀቂያ ወረቀት ለመቀበል ማመልከቻ አቅርበው  የተፈቱ ናቸው።  አፕሊኬሽኖች እንዴት እንደሚገመገሙ  እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ግልጽነት የለ የእስር ጊዜያቸው እየጨመረ ከመሄዱም  ባሻገር የሚያቀርቡት ይግባኝ  በድግግሞሽ ውድቅ ይደረጋል።  እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በጥናቱ ላይ ከሚገኙት እስረኞች 80 በመቶ ያህሉ ማመልከቻቸው ቢያንስ ሶስት ጊዜ ውድቅ ተደርጎባቸዋል

 

 ይግባኝ ያቀረቡና  ማመልከቻቸው የተሳካላቸው አመልካቾች በሚለቀቁበት ጊዜ ከፍተኛ ገደቦች ያጋጥማቸዋልሥራ መሥራት፣ የባንክ አካውንት መክፈት፣ ስልክ ማግኘት ወይም ያለፈቃድ የመኖሪያ አካባቢያቸውን መልቀቅ  በጭራሽ አይችሉም።  ብዙዎች የተፈቱ እስረኞች ለመሥራት አይችሉም ይህም ማለት ጊዜያዊ የመልቀቂያ ወረቀት ሲሰጣቸው  የፈረሙበትን ሁኔታዎችን ማክበር በተግባር ጸም ግድ ይላቸዋል።ታናካ እንደሚሉት  “ፍፁም ከእውነታው የራቀ ገደብ ነው” ለዋል።  "ከሰብአዊ መብት አንፃር አንድን ሰው የመስራት አቅሙን መንፈግ ከባድ ጥሰት ነው ብዬ አስባለሁ።"  ሲሉም አክለው ገልፀዋል።በጊዜያዊነት የሚለቀቁት እስረኞች ሲሰሩ ወይም ከአካባቢያቸው እርቀው ከተገኙ ጥብቅ ውሎቹን በመጣስ ተብለው  ወደ ማቆያ ማእከላት ይመለሳሉ።

 

 ስለዚህ እርግጠኛ አለመሆን፣ ፍርሃትና ግራ መጋባት የስደተኞቹን ሁኔታ ፍንትው ብሎ ከማሳየቱም ባሻገር የተሰበሰቡት  ተሞክሮዎችl

ማስረጃዎች  ይህንን  የሚያሳዩ ናቸው።በንድፈ ሀሳብ ደረጃ እስረኞች ከውጭው አለም ጋር የመግባባት መብት ሲኖራቸው የኢሚግሬሽን ቢሮ ስለታሰሩበት ሁኔታና ስለ ማመልከቻቸው ሁኔታ መረጃ የመስጠት ግዴታ ቢኖርበትም፣ በዚህ በኩል መረጃ ሰብሳቢዎቹ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።በተግባር መረጃ የማግኘት መብት በጣም የተገደበ እንደሆነም  አስረድተዋል።  እስረኞች የክፍያ ስልኮችና የ30 ደቂቃ የእስረኛ ጉብኝቶች ከውጭው ዓለም ጋር ብቻ የሚገናኙ ብቸኛው  የእስረኞቹ ፍቃድ ማግኘት ብቻ ናቸው።  የኡሺኩ ኖ ካይ ዘገባ እንደሚያስረዳው እስረኞቹ በአጠቃላይ እንደ መታሰራቸው ህጋዊነት፣ የሚቆዩበት ጊዜ፣ የመግባቢያ መብታቸው ና የእስር መቃወሚያ ህጋዊ መንገዶችን በመሳሰሉት ነገሮች ላይ መረጃ  ጠይቆ እንዳያገኝ  መደረጉ ተገልጿል

 

 " እስረኞች እንዴት መውጣት እንዳለባቸው አያውቁምለምን ያህል ጊዜ በእስር እንደሚቆዩም አያውቁምለመውጣት ምን እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው አያውቁምስለዚህ ብዙ ድንጋጤ አለ፣ ብዙ ፍርሃት አለ” ሲሉ በጃፓን የስደተኞችን የምርምር ፕሮጀክትና የድጋፍ መርሃ ግብር የሚመሩ በቶኪዮ የሶፊያ ዩኒቨርሲቲ የባህል አንትሮፖሎጂስት ፕሮፌሰር ዴቪድ ስላተር ያስረዳሉ።  ስላተር(Slaterተማሪዎቹ ከቀድሞ እስረኞች ጋር የቪዲዮ ቃለ ምልልስ አድርገዋል

 

ከዲፕሎማት መጽሔትና ጋዜጣ እንዲሁም ድረ ገፅ ጋር ባው  ቃለ መጠይቅ ከናይጄሪያ የመጣ አንድ ስደተኛ እስረኛ ስበእስር ቤት ውስጥ ስላለው  ሁኔታ ሲናገር የኢሚግሬሽን ቢሮክራሲውን ለመረዳት እርስ በእርሳቸው እንዴት እንደሚረዳዱ እንዲህ በማለት  ገልጿል “ብዙ አዲስ መጤዎች ወደ እስር ቤት ሲገቡ ስለ አሠራሩ  ምን እንዶሆነ የእስር ቤቱን ምንም አያውቁም። ሌላው ቀርቶ አንድ ሺህ ዶላር ከፍለው ለጊዜያዊ  መልቀቅ ማመልከት እንዳለባቸው እራሱ አያውቁም።  ስለ ዋስ ሰጪዎች፣ የሚቆዩባቸው  ቦታዎችና ስለዛ ሁሉ አያውቁም።  ስለዚህ ስርዓቱን የምና እስረኞች አዲስ መጤዎችን ማስተማር እንችላለን።  ስደተኛው እስረኞቹ ከኢሚግሬሽን ኦፊሰሮች መረጃ ሊጠይቁ ቢችሉም  ኦፊሰሮቹ መልስ የላቸውም ብለዋል።''በተለምዶ መኮንኖቹ ለታሳሪዎቹ ምንም ነገር ለማስተማር ፍቃደኞች አይደሉምም ይህንንም አይሞክሩ ” ብሏል።

 

 በምስራቅ ጃፓን የኢሚግሬሽን ማእከል ከአራት እስከ አምስት ሰዎች ፍጹም የተለያየ ባህል ካላቸው እንግዶች ጋር በትናንሽ ክፍሎች ውስጥ አብረው ታስረዋል።  የሞባይል ስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት የላቸውም፤ ጊዜውን ለማሳለፍ ብቸኛው አማራጭ ቴሌቪዥን ነው።  የግላዊነት እጦትና የረጅም ጊዜ እስራት ጭንቀት በእስረኞች መካከል የማያቋርጥ ውጥረት ያስከትላል።  ናይጄሪያዊው ስደተኛ ከስሌተር የምርምር ቡድን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የእስር ቤት ሰራተኞች እስረኞች እራሳቸውን ሊጎዱ የሚችሉ እንደ ረጅም ገመዶች ወይም የብረት መቁረጫዎች ያሉ ማንኛውንም ነገር እንዳያገኙ እንደሚደረግ በዝርዝር ገልጿል።  "ሁሉም ሰው በጭንቀት ውስጥ ነው" ሲል ተናግሯል።

 

 የኡሺኩ ኖ ካይ የምርመራ ዘገባ በረጅም ጊዜ እስራትና በአእምሮ እንዲሁም  በአካል ጤና ችግሮች መካከል ያለውን ግልጽ ግንኙነት አጉልቶ ያሳያል ይህም ከፍተኛ መጠን ያለው የልብ ህመም፣ የደም ግፊትና የአካል ክፍሎች ድክመትና የሰውነት መዛልን ይጨምራል።  ሪፖርቱ የኢሚግሬሽን ቢሮን ተቋማዊ የህክምና ቸልተኝነትን በመክሰስ የቶኪዮ ክልል ኢሚግሬሽን ቢሮ የታመመ ኩርዳዊ እስረኛ ወደ ሆስፒታል ለመላክ ፈቃደኛ አለመሆኑን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ቀደም ሲል በጃፓን ታይምስ የተዘገበውን ገልጿል ።  


እስካሁን ድረስ ቢያንስ 15 የውጭ ዜጎች በባለስልጣናት ሲጓጓዙ ወይም ሲታሰሩ የሞቱ እንዳሉ የሚታወቁ ጉዳዮች አሉ።

 

በኤፕሪል ወር ጃፓን ብዙ የውጭ አገር ሰራተኞችን ወደ ሀገሯ ለማስገባት ያለውን የሀገሪቱን የሰራተኛ እጥረት ለመቅረፍ እንደ አንድ ስትራቴጂ አካል በመቁጠር ፈቅዳ ነበር።ይህ ላልተማሩ ወይም ለጉልበት ሰራተኞች አዲስ ቪዛ አስተዋወቃ  ነበር።  ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጥገኝነት ጠያቂዎች አያያዝ ይበልጥ እየጠነከረ ቀጥሏል።  በጊዜያዊ ወረቀት መፈታት ሲሰሩ የተያዙ ስደተኞች  ቢያንስ በሶስት አመት ከሶስት ወር እስራት እንደሚቀጡ  ጠበቆቹ ጠቁመዋል።  ታናካ እንደሚሉትጃፓን በእርግጥ የውጭ አገር ሠራተኞች ያስፈልጋታል።  ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የሚቃረን ፖሊሲ ነው  ያለው ።" ሲሉ ተናግረዋል።

 

 

በጊዜያዊ የመልቀቂያ ወረቀት ስርዓት ውስጥ የበለጠ ተለዋዋጭነት እንዲሚታይ ገልጸው ወደፊት እንደሚሻሻል  ተስፋ አድርገዋል።"ጊዜያዊ የእስረኛ  መለቀቅን ለረጅም ጊዜ  እንዲሻሻል በትጋት እያደሱ ያሉ ወገኖች አሉበጃፓን የተፈቱ እስረኞች ሕይወታቸውን በአግባቡ እንዲመሩ ቪዛ ሊሰጣቸው ይገባል፤›› ብለዋል።

 

 

ታናካ በምስራቅ ጃፓን የኢሚግሬሽን ማእከል የረሃብ አድማ እንዴት እንደሚከሰት መገመት እንደማትችል ተናግራለች።  በእርግጥ የኢሚግሬሽን ቢሮ የረሃብ አድማውን እንዲያቆሙ ና ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ይፈልጋ
።  እንደ አለመታደል ሆኖ በአሁኑ ወቅት ይህ የሚሆን አይመስልም።

Comments

Popular posts from this blog

ብሄርና ዘረኝነት የነገሰባት ሀገር

ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ቻይናውያን ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ

በሁለት የተከፈለው የወያኔ መንግስትና በሀገሪቱ ላይ የጫረው እሳት