የጃፓን የታሰሩ ጥገኝነት ጠያቂዎች ተስፋ መቁረጥ
ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ) እ.ኤ.አ. ከ2015 የአለም የስደተኞች ቀውስ ወዲህ በግሎባል ሰሜን ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩኤንኤችሲአር) እንዳስታወቀው ካለፈው አመት ጀምሮ በአለም ላይ 79.5 ሚሊዮን ሰዎች በግዳጅ ከሀገራቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ነበሩ። ከእነዚህ ሰዎች መካከል 4.2 ሚሊዮን የሚሆኑት ጥገኝነት ጠይቀዋል። በምላሹ፣ የግሎባል ሰሜን ያደጉ ሀገሮችና በ ኢኮኖሚዎች ከፍተኛ ደረጃ ወደ ደረሱ ሀገሮች ቢሰደዱም ሀገራቶቹ በጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ያላቸውን ገደቦች አጠናክረዋል። እ.ኤ.አ. በ2019 በተደረገው ጥናት ጃፓን ሀገር ላይ ከ10,000 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ጥገኝነት ጠይቀዋል። ከ12 ወራት በላይ የሚቆይ ረጅም የጥበቃ ጊዜ ማድረግ በጃፓን የተለመደ ነው በተለይም ለስደተኛነት ሁኔታ ላመለከቱ የውጭ ሀገር ሰዎች ። (በንጽጽር፣ ዩናይትድ ስቴትስ በ2018 ከ97,000 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች ነበሯት። በጃፓን ውስጥ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ስለረዥም ጊዜ መታሰራቸው ቃለ መጠይቅ ሲደረግ በአሜሪካ ወደ 42,000 የሚጠጉ ሰዎች በኢሚግሬሽንና በጉምሩክ ማስፈጸሚያ ተይዘው ታስረዋል።) የኢሚግሬሽን አገልግሎት ኤጀንሲ (ኢሳ) የምስራቅ ጃፓን ማቆያ በኡሺኩ፣ ኢባራኪ ግዛትና የቶኪዮ ማቆያ እስር ቤትን በመጎብኘት ለረጅም ጊዜ በእስረኞች መካከል የረሃብ አድማ በፍጥነት መስፋፋቱን በርካታ ጋዜጠኞች ለመመልከት ችለዋል ። ይህ መጣጥፍ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በረጅም ጊዜ እስራት ውስጥ ያለውን ችግር ለማሳየት ይፈልጋል። ማንነታቸውን ለመጠበቅ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ በሙሉ የውሸት ስሞች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተ