Posts

Showing posts from October, 2022

የእርስ በርስ ጦርነቱን ለማስቆም ተደራዳሪዎቹ ፊርማ ተፈራረሙ

Image
ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ (ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሀያሲ )            *የአፍሪካ ህብረት የሽምግልና ቡድን መሪ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ የስምምነቱ አፈፃፀም በአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ቡድን ቁጥጥር እና ክትትል የሚደረግበት ነው ብለዋል።  ሂደቱን የአፍሪካ ችግር ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄ ነው ሲሉ አድንቀዋል።  * የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ አቶ ሬድዋን ሁሴን እንዳሉት ሁሉም ወገኖች በስምምነቱ ላይ ያለውን አቋም እና የሰላምን መንፈስ አክብረው  መጓዝ  አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።  * የትግራያ አማፂ  ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት ምላሽ በክልሉ ስለደረሰው መጠነ ሰፊ ሞትና ውድመት ተናግረው ሁለቱም ወገኖች የገቡትን ቃል እንደሚያከብሩ ያላቸውን ተስፋ  ገልፀዋል  ።    የኢትዮጵያና የትግራይ አማፂያን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ። ብሎምበርግ  እንደገለፀው የኢትዮጵያ ና የትግራይ አማፂ ቡድን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነው  የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የደረሱት። የትግራይ አማፂ  መ ቡድን መሪዎችና የኢትዮጵያ መንግስትና አጋሮቹ  መካከል በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈው የተኩስ አቁም ስምምነት  ዳግመኛ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ግጭት ማብቂያ አሁን ሊሆን ይችላል የሚል ተስፋ ሰንዝሯል ብሏል።    የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የአፍሪካ ቀንድ ዋና ተጠሪ በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ  ዛሬ ማምሻውን ባሰጡት መግለጫ  “በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉት ሁለቱ ወገኖች ጦርነቱ እንዲቆም በይፋ ተስማምተዋል” ብለዋል።  "ይህ ጊዜ የዚህ ሂደት መጨረሻ አ