እነ አሳማዎች!
✅ እነ አሳማዎች! ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራዘአራዳ) «የጠገበ አሳማ ከመሆን የራበው ሰው መሆን እጅግ የተሻለ ነው።» የሚለውን አባባል የተናገሩት ተዋቂው ፈላስፋ ስቱዋርት ሚል እና ፕሌቶ ናቸው።እንደ ስቱዋርት እና ፕሌቶ አገላለጽ ይህ አባባል የተጠቀሙት ተዋቂው ፈላስፋ ሶቅራጥስ ብዙ እያወቀ ነገር ግን እንደሌሎቹ እራሱን አዋቂ ነኝ እያለ ሳይኮፈስ እንአላዋቂ ሆኖ የተገኘ ፈላስፋ ስለነበረ ነው። ለዚህም ነው ስቱዋርት ሚል «የጠገበ አሳማ ከመሆን የራበው ሰው መሆን እጅግ የተሻለ ነው።»ያለው።ይህንንም ሲያብራራ« የጠገበ ሰነፍ ሰው ከመሆን ደግሞ የተራበ ሶቅራጥስ መሆን በጣም ይሻላል።አሳማውም ሆነ ሰነፉ ሰው የሚኖራቸው የራሳቸው ሐሳብ ብቻ ነው። በአንፃሩ ግን በሁለቱም ወገን ያለውን ሐሳብ በሚገባ ያውቁታል። »በማለት ይገልጸዋል።በእርግጥም ሆዱን ከቆለለ ማህይም ሀብትም ይልቅ።ምንም የሌለው ብዙ ለማወቅ የሚጥር፤ራሱን እንደ አላዋቂ የሚመለከት ፈላስፋውን ሶቅራጥስ አይነት ደሀ መሆን ይሻላል ነው ያለው ስቱዋርት ሚል ። የፕሌቶም አስተሳሰብ ሰው የቱንም ያህል የምግብ ፍላጎት(ሥጋዊ ጥያቄው)ተሟልቶ ሞራላዊውን ጥያቄ ካልመለሰ ወደ እንስሳነት መውረዱ አይቀሬ ነው ይላል። እንዲያውም ፕሌቶ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሲናገር «ከጠገበ አሳማ የራበው ሶቅራጥስ ይሻላል » በማለትም ገልጿል። ልክ እንደ ሶቅራጥስ ባንሆንም ብዙዎቻችን በዕውቀት የተራብን እንኖራለን።ብንማር የማይሰለቸን ፤አሊያም ለማወቅ ያገኘነውን ሳንመርጥ ብዙ ማንበብ የምንፈልግ ሰዎች ብንኖርም ያነበብናትን ትንሿን ወይንም ቁንጥሯን ዕውቀታችንን ይዘን ግንብዙ የምናወራ በርካቶች ነን።ስለ ፖለቲካ ሲወራ ተዋቂ ፖለቲከኛ፤ስለ ማህበራዊ ሕይወት ሲወራ የማህበራዊ ሕይወት ጠበብት ወይም ሀያሲ ፤ስለ ስፖርት