Posts

Showing posts from October, 2019
Image
እግዚአብሔር ለሀገራችን ሰላሙን ያውርድልን! ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን(ደራሲ፣ተርጓሚ፣የታሪክ አጥኝና የቋንቋ ሊቅ) ከበፊት ጀምሮ ከማደንቃቸው ጸሐፍቶች ማካከል አንዱ ናቸው።  በሚያነሷቸው ርዕሰችና ነጥቦች  የበርካታ ተደራሲያንን ቀልብ መሳብም ይችላሉ። ደፋር ናቸው  እስካሁን ድረስ በስደትም የቆዩት ይኸው ደፋርነታቸው ይመስለኛል።    ፕሮፌሰር ጌታቸው በኢትዮጲስ ጋዜጣ የምሁራን መድረክ የሚለው አምድ ላይ ቋሚ አምደኛ በመሆናቸው እኔም  ጋዜጣዋን በየሳምንቱ ስለምገዛት  የሚጫጭሩትን ሀሳቦች ብዙውን ጊዜ አነባላው ።  መቼም ውጭ ስላሉ በዚህ ድህረ ገጼ ወይንም ብሎጌ ላይ መልዕክቴ በቀጥታ ይደርሳቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።   ቀድሞ የሀገራችን መሪ በነበሩት በኮሎኔል መንግሥቱ፣በአቶ መለስና በአቶ ኃይለማርያም አስተዳደር ጊዜና በአሁኑ ወቅት ደግሞ በዶክተር አብይ አስተዳደር ጊዜ በመገናኛ ብዙሐን የሚያነሷቸው ሀሳቦች በጣም አራምባና ቆቦ ሆኖ ነው ያገኘሁት ።ያ ደፋርነታቸውና ሚዛናዊ የሆነ አስተያየታቸው ጠፍቶ ነው ያየሁት። ምናልባት አንዳንዴ እድሜ እየገፋ ሲመጣ መዘንጋት ብቻ ሳይሆን የፍራቻ መንፈስም አብሮ ስለሚመጣ ከዛ የመነጨ ነው ብዬ እንዳልደመድም አሁንም በስደት ላይ ነው የሚገኙት።    ከሀገራችን ተሞክሮ ስነሳ ዘራፍ ይል የነበረው ወጣቱ ትውልድ እንደዛሬ ብሄርተኛ ሳይሆን በፊት ለሀገሩ ከእሱ የሚጠበቀውን ያደርግ ነበር ። አሁን ግን እንደዛ አይደለም ብሄርተኛነት የተጠናወተ ጭፍን በግ ሆኗል።   የጦር መሪና አዋጊ የነበረው ደግሞ ትዳር  መስርቶ ልጆች ማፍራት ሲጀምር በፊት ከተነሳበት ዓላማና ግብ ወደ ኋላ ማፈግፈግ  ይጀመረበት ወቅት ላይ ደርሰናል። እንዲያውም አብዛኛው የኅብረተሰብ

ፍቃዱ ማህተመወርቅ በቆየ ክስ ጥፋተኛ ተባለ-ዘብጥያም ገባ

Image
ፍቃዱ ማህተመወርቅ  በቆየ ክስ ጥፋተኛ ተባለ-ዘብጥያም ገባ   ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ  የዶክተር አብይ መንግሥት ስልጣን ላይ ከወጡ ከ2010 ዓ/ም በኋላ  በርካታ የተዘጉ ድህረገጾችና ብሎጎች ተከፍተዋል።የታሰሩ ጋዜጠኞችና  የፖለቲካ አመራር  አካሎች እንዲሁም በአሸባሪ የተፈረጁ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሚዲያዎች ወደ ሀገር ቤት ሰላማዊ ትግል እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸው በሀገር ቤት ውስጥ በአሁኑ ወቅት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ።ይህ በጎና ተስፋ ሰጪ ሁኔታ  ቀጣይነት ይኖረዋል የሚል ተስፋ ጭሮ ነበር።   በየአመቱ በሚወጣው የሚዲያ ነፃነት ደረጃ ኢትዮጵያ በሚዲያ ነፃነት ከበፊቱ ትንሽ ደረጃዎችን በማሻሻል የ110ኛ ስፍራን ይዛም ትገኛለች  ።  ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ትንሽ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ኢንተርኔት ወይንም ሴሉላር ዳታ ከሥራ ውጪ እስከመሆን የደረሰበት ሁኔታ መኖሩን ለመመልከት ችለናል።በተለይም ከሰኔ 15 ቀን የአዲስ አበባና የባህርደር ከተከሰተው አሰቃቂ ግድያ በኋላ ኢንተርኔት ቤቶች ተዘግተዋል ሴሉላር ዳታዎች ሥራቸውን አቋርጠው ተመልክተናል።    ከዚህ ሌላ ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልኩ የሽብር ክስ ተመስረቶባቸው ዘብጥያ የወረዱ ንጹሀን ጋዜጠኞችም አሉ።    ከነዚህም መካከል  የኢትዮጲሱ ጋዜጠኛው ምስጋናው ታደሰ ፤ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ፣ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ፣ እና ሌሎችም ጋዜጠኞች የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ይገኛሉ።   ትናትና ደግሞ በ2006 ዓ.ም የገዥው የወያኔ መንግሥት በአምስት መጽሔቶችና በአንድ ጋዜጣ ላይ ክስ መሥርቶ እንደነበር አይዘነጋም።   በወቅቱ በርካታዎቹ ለስደት የተዳረጉ ሲሆን በስደት ጎረቤት ሀገር ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል የ

ሥጋት ያንዥበበት አገራዊ ምርጫ !

Image
ሥጋት ያንዥበበት አገራዊ ምርጫ !  ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ     እንደምን አላችሁልኝ ውድ አንባብያኖቼ ለመሆኑ ስለ ተርቡት(ተርብ)ምን ያህል እውቀቱ አላችሁ?ብዘዎቻችሁ እከሌ እኮ ተርቡት(ተርብ)ነች ሲባል ሰምታችሁ ይሆናል።   ተርቡት(ተርብ) የምትባለው በራሪ ነፍስ ስትሆን እንደ ማር ዐይነት ታበጃለች ነገር ግን በውስጡ ምንም አይገኝበትም ።በቤቷም ውስጥ በያይነቱ   ትል ይገኛል።በመና(ን)ደፍም   ከንብ እጅግ ትከፋለች ፤ መርዟ ከሷ አይለይምና   ...የተርብ እንጀራ የበላ ውሻ ክፉ ይኾናል።     እናም እከሌ እኮ   ተርቡት (ተርብ) ነች ካለን እንደ ሴቶች ትጠምቃለች ፣ትጋግራለች ፣ድግሷ ጣዕም የለውም   ፣ ባሏ ቢመታትም መልሳ ትመተዋለች ፤ አሸር ባሸር ሰርታ «ከፈለክ ብላ ካልፈለክ ተወው » ብላ ታቀርባለች፤ በመሰናዶዋ ሁሉ ጉድፍ ይገኝባታል።       ለወንድ ብዙ ጊዜ ቃሉን ባንጠቀምበትም ። ቃሉን ያለቦታው እንሸነቅርና ሌላ ትርጉም ሲሰጠው እንሰማለን «እከሌ ተርብ ነው » እንልና ጎቦዝ ሥራ ላይ ፈጣን እንደሆነ ተልኮ ፈጥኖ የሚደርስ የሚመስለን   በርካቶች ነን ። ከላይ ከቀረበው ትርጓሜ አንፃር ግን ተርቡት(ተርብ) የምንለው ክፉ የሆነ፣ ጨቅጫቃ፣ በሥራው ስውን የማያረካ ፣ቶሎ ተናዳጅና ለፀብ ቶሎ የሚፈጥን ሰው ወዘተ. የሚል ትርጉም እናገኛለን።   ከተርቡት(ተርብ) የባሰም አለ ዝንቡት (ዝንብ) ይህን ቃል ከላይ እንደተጠቀሰው ለወንድ ሳይሆን ለሴት ነው የምንጠቀመው «እከሌ እኮ ዝንቡት ነች ! » ካልን ካገኘችው ወንድ ጋር የምትተኛ ሴት ወይንም አመንዝራ ሴት ነች። እንደማለት ይቆጠራል።   እንደሚታወቀው ዝንብ ከማንኛውም እንስሳ ላይ   ቁስልና መግልን ደምና ዕድፍን ሁሉ የምትቀስም ናት ያረፈችበት ነገር ሁ

እነ መስሎ አደሮች !

Image
u     እነ መስሎ አደሮች !    ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ   ደምሴ በትረ ስልጣኑን ለ28 አመታት ያለ ተቀናቃኝ ይዞ ሀገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው የወያኔ/የኢሕአዲግ  መንግስት በፊት እሱን የሚቃወሙ ሁሉ  አንዴ ደርግ /ኢሠፓ እርዝራዦች ፤ ሌላ ጊዜ  የደርግ/ኢሠፓ     አፈቀላጤና   ናፋቂዎች   ፤ሌላ ጊዜ የ ቦዜኔዎች ስብስብ ፤ሌላ ጊዜ የጫት ማህበር ስብስብ ፤ሌላ ጊዜ ሥራ ፈቶች ወዘተ ብላ ብላ ..እያለ   እያለ የነፃው ፕሬስ   አባላትንና ተቃዋሚ የሆነውን በሙሉ ያለግብራችን ተለጠፊ ታፔላ  ሲሰጠን ቆይቷል።   መቼም ውጭ ሀገር ሆኖ መጻፍና ማውራት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ከሚጽፈው ጋር በሚዛን ቢለካ ልዩነቱ ከፍተኛ በመሆኑ እንደ ሽንታም     ስለሚያስቆጥር   ውጪ ሆኖ መጻፍን አልፈለኩትም ነበር ...   ተሳሳትኩ ?...   ጁቡቲን እረግጦ የማያውቅ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ ያየ ይመስል "  ተወው እባክ እሱ ድራፍቱን እየጠጣ፤ እየተዝናና ... ነው ሥራ ፈት ሆኖ የሚቸከችከው ..."  የሚሉ የወሬ አቅማዳ ተሸክመው የሚዞሩ ለሆዳቸው ያደሩ ። እነ መስሎ አደሮች ወይንም በሌላ አነጋገርየእነ አጋሰሶች የቡና መጠጫ ነው የምንሆነው   ።    ደግሞ እኮ አሁን  የፕሬስ መብት ተከራካሪዎችም ለኢትዮጵያ ያላቸውን አድናቆት እየገለጹ ልንአይደል ?ካካካካ...   መቼም   አድናቆት ከተገለጸ አይቀር እንደው እስካለው ድረስ በፊት ብሎጌ ላይ አሁን ደግሞ መጽሔት ላይ ጦማሪ ሆኜ መቀጠልንመርጫለው      ..ተሳሳትኩ ጎበዝ!…    እንደኔ አይነቱ ክርስቲያን ደግሞ   መቼም ውሸት  አያምረበትም !     ደግሞ እኮ   መሪያችን ክቡር   ዶክተር   ጠቅላይ ሚኒስትር ... .,   ክርስቲያን አይደሉ ! ያውም