Posts

Showing posts from November, 2023

ፌደራሊዝም ምንድን ነው? ለምንድነው ኢትዮጵያ ይህንን ርዕዮት ዓለም የምትጠቀመው? ለምንስ ፍፁም ልትሆን አልቻለችም?

Image
 ከወሰንሰገድ  መርሻ (ከጮራ ዘአራዳ) በሀገራችን ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከማሳዘን አልፎ ወደ ባሰ እረመጥ ውስጥ ሀገራችን እየገባች መሆኑ ሁላችንንም የሚያሳዝነን ነው። ሀገራችን የምታካሂደው ርዕዮት ዓለም ፌደራሊዝም ምንድን ነው?  ለምንድንስ  ነው  ኢትዮጵያችን  ይህንን ርዕዮት ዓለም የምትጠቀመው? ለምንስ በዚህ ርዕዮት ዓለም ፍፁም ልትሆን አልቻለችም?  በዚህ ዙሪያ በዛሬው መጣጥፌ አንድ ለማለት ወደድኩ።።እንደምን ከረማችሁልኝ ውድ አንባቢያኖቼ። ለመሆኑ  ፌደራሊዝም ምንድን ነው ? ፌደራሊዝም ሥልጣን በማዕከላዊ ባለሥልጣንና በትናንሽ የክልል መንግሥታት መካከል የሚከፋፈልበት የመንግሥት ሥርዓት ነው። ብዙ አገሮች በድንበራቸው ውስጥ ያለውን የብሔረሰቦች ልዩነት ለመቆጣጠር እና አንድነትን ለማጎልበት ፌዴራሊዝምን ይቀበላሉ። በአለም አቀፍ ደረጃ 25  በመቶ የሆነው የፌደራል ሀገራት ያሉ ሶሆን  40% የሚሆነውን  የአለም ህዝብ ይህ ርዕዮት ዓለም ተከታዮችን እንደሚወክል የጥናቱ አቅራቢዎች ይናገራሉ። ፌዴራሊዝም ክልሎች  ቢሆኑም የዋናው  ሀገራቸው አካል ሆነው አንዳንድ ጉዳዮቻቸውን - ለምሳሌ ትምህርትን ወይም የስራ ቋንቋን በሚመለከቱ ውሳኔዎች እንዲመሩ ያስችላቸዋል። ኢትዮጵያችን  ፌዴራሊዝምን የተቀበለችው በወያኔ ጊዜ በ1991 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) - የአራት ትላልቅ ፓርቲዎች ጥምረት - ስልጣን በያዘ ጊዜ ነው። ይህም ከ1974 እስከ 1991 ሀገሪቱን ሲመራ የነበረውን የኮሚኒስት ወታደራዊ መንግስት ደርግን ከስልጣን ለማውረድ ለ17 አመታት የዘለቀው ህዝባዊ አመጽ ማብቃቱ ከተበሰረ በኋላ ነው። በእኔ እይታ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ የተሻለው አካሄድ ሆኖ ቀጥሏል። ወይስ  አልቀጠለም ብሎ ለመናገር ቢከብድም። የባህል እና የቋን