Posts

Showing posts from November, 2019

በኢትዮጵያ- ውያኔ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቀ

በዶክተር አብይ የሚመራው አዲሱ የኢህአዲግ የብልጽግና ፓርቲን  የሚቃወመው የትግራዩ ፓርቲ ወያኔ የኦዲፓ፣የአዲፓ እና የደቡብ ሕዝቦች ዲሞክራሲ ፓርቲ ያቋቋሙት የብልጽግና ፓርቲ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በዶክተር ደብረፅዮንና በአቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ይፋ አድርጓል።   በተለይም ዶክተር አብይ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ቡርቱካንን የሾሞት ለዚሁ ማስፈፀሚያ እንደሆነና ገና አዲሱ የብልጽግና ፓርቲያቸው  እውቅና በምርጫ ቦርድ ሳይሰጠው ከሕገ መንግስቱ እውቅና ውጭ ፓርቲውን ይፋ ማድረጋቸው  ሕገወጥ ተግባር መሆኑን የሕወአት አመራሮቹ ገልጸዋል።   አቶ ጌታቸው እንደሚሉት ሌላው ቀርቶ ሀገሪቷ ሰላምና መረጋጋት በለሌበት ሁኔታ ምርጫው እንዲካሄድ መደረጉ ተገቢ ካልሆነም ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቱን ሳላም ሳያደርጉ ዳግመኛ ቶሎ ብሎ ፓርቲ አቋቁመው ወደ ስልጣን መምበሩ በማናለብኝነት ለመቆናጠጥ ያላቸው ፍላጎታቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል።   አቶ ጌታቸው ለድምፀ ወያኔ ቴሌቪዥን እንደገለፁት ፓርቲያቸው በርካታ ሰተቶች ቢኖርበትም በርካታ ስራዎች መስራቱን ገልፀው የአሁኑ መንግስት ግን ከሥራ ይልቅ የሕዝቡን ችግርና ብሶት ከመፍታት ይልቅ ወሬና አሉባልታ ላይ በማተኮር በማናለብኝነት ላይ ያተኮረ በመሆነ ሀገሪቱን የሚያስተዳድር ከሁሉም ፓርቲዎች ውጭ የሆነ ገለልተኛ የሆነ የሸምጋይ ወይንም የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ  ቅድሚያ ለሀገሪቱ  ሰላምና መረጋጋት ተሰጥቶ  ይህ ከተከናወነ በኋላ ወደ ምርጫው እንዲገባ አሳስበዋል። አለዛ ግን ሀገራችን ወደ ባሰ ትርምስና ብጥብጥ ልትገባ እንደምትችል ፍራቻቸውን ከወዲሁ ሳይገልፁ አላለፉም።

በሁለት የተከፈለው የወያኔ መንግስትና በሀገሪቱ ላይ የጫረው እሳት

ወያኔ በሁለት ከተከፈለ ሰነባበተ አሁን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው  የብልጽግና ፓርቲና ሀገሪቱን ላለፉት 27 አመታር በበላይነት የሚመራው የወያኔ አመራሮች ከፓርቲው ማፈንገጥ በሀገሪቱ ውስጥ በአንድ በኩል መልካም ዜና በሌላ በኩል ለስልጣን በሚደረገው እሩጫ የበርካታ ሕይወቶችን እንዳይቀጥፍ ከወዲሁ ተፈርቷል።   በቅርቡ በተለያዩ ክልሎች በተቀሰቀሰው ብጥብጥ ለበርካታ ሰዎች መሞትና  መሰደድ መንስ ኤም የሆነው ይሄው ነው።   የሁለቱ ወገኖች ፍጥጫ ከቃላት ልውውጥ አልፎ ወደ ሌላ አቅጣጫም እየሄደ ይገኛል። ወደ ፊት ደግሞ ከዚህ የበሳ ችግር ሊፈጥር ይችላል።  በተለይም በርካታ ሰራዊት ያለውን የደርግ መንግስት ጋር ከሻዕቢያ ጋር በመሆን የገረሰሰው ወያኔ ከሶስቱ ጥምር ፓርቲዎች በተሻለ መልኩ በወታደራዊ ስልት የተሻለ አቅም አለው።ከዚህ ሌላ ሙሉ ለሙሉ የትግራይ ሕዝብ ድጋፍ አለው።  አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለይምስል ዶክተር አብይን ይደግፍ እንጂ ሁሉንም ወገኖች አይፈልግም ። ስለዚህ በመሐላቸው እሳት ቢነሳ ሕዝብ እንደጭድ ከመታጨድ ይልቅ ተመልካች ሆኖ ማሳለፍን ሊመርጥ ይችላል።ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ወደ ባሰ ችግር ውስጥ ሊከታት ይችላል ይህ የአብዛኛው  የፖለቲካኞች ተንታኞች ፍራቻ  ነው። ሻዕቢያና ወያኔ የትግራይ ትግርኛ ፓርቲ እንዳይመሰርቱ አሁን እሳትና ጭድ ናቸው።  ትግራይ ራሷን ገንጥላ የራሷን መንግስት መሥርታ የመጓዝ አቅሙም ሆነ ኃይሉ አላት።ይህ ግን የሚሆነው ከመሐል መንግስት ጋር ያለው የፖለቲካ ጡዝት ከበረደ ብቻ ነው።አለዛ ግን ወደ ባሰ ዕልቂት ያመራል ተብሎ ተፈርቷል።

ወያኔና ዶክተር አብይ እሳትና ጭድ ሆነዋል 

Image
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና   ስልጣን ላይ እንዲወጡ ቁልፉን ሚና ከተጫወቱት መካከል በዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው የትግራዩ ወያኔ አሁን ካለው ከዶክተር አብይ መንግስት ጋር በአሁኑ ወቅት እሳትና ጭድ ሆነዋል።   የትግራይ ሕዝቦች አርነት ግንባር(TPLF)ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የኢህአዲግ አባሎች መካከል   አንዱና ዋንኛው ሲሆን ከአፕሪል 2018 እ.ኤ.አ ጀምሮ ስልጣን ላይ የወጡትን ዶክተር አብይን አካሄድ በተቃራኒ መልኩ የሚቃወም ድርጅት ነው። ፓርቲው ከትግራይ በሚያሰራጨው በድምፀ ወያኔ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ላይ ይህንኑ አመለካከታቸውን በመግለጫና በተለያዩ ዜናዎቹ ሲቃወም ይታይል ።ለምሳሌ ሰሞኑን ዶክተር አብይ ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉትን ውህደት አስመልክተው በትዊተር ገጻቸው ላይ በእንግሊዘኛ፣በኦሮምኛ እንዲሁም በአማርኛ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት «በተዋሐደዉ ፓርቲ ሕገደንብ ላይ ሰንወያይ ቆይተን አጽድቀን ወደ ምክር ቤቱ እንዲመራ ወስነናል። የሦስቱም ቀናት ውይይታችን ግልጽና ደሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ተካሂዷል። ውይይቱ ይበልጥ አመራሮቹን ያቀራረበ ሆኖ በመጠናቀቁ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል።» ካሉ ከቀናት በኋላ «የኢሕአዴግ ምክር ቤት ዛሬ የፖርቲውን ውሕደት አጽድቋል። በአዲሱ የብልጽግና ፓርቲ አማካኝነት ሁሉም የታላቋ ኢትዮጵያ ዜጎች የሚሳተፉበት ጠንካራ፣ አካታችና እውነተኛ የፌደራል ሥርዓት ለመፍጠር ቆርጠን ተነሥተናል። ጸንተንም እንታገላለን ።»በማለት አክለው ገለጸው ነበር። ይህንኑ በመንተራስ የመገናኛ ብዙሀንም   ሲያርግቡ ቆይተዋል። ደምፀ ወያኔ ግን   በቴሌቪዥኑ ላይ   በአማርኛ ባሰራጨው ዘገባ ዶክተር አብይ «የኢሕአዴግ ምክር ቤት ዛሬ የፖርቲውን ውሕደት አጽድቋል..» ፤«..አመራሮቹን ያቀራረበ ሆኖ ..» በማለት

ደብቡ ኮሪያ ግብፅን በአባይ ግድብ ዙሪያ ለመርዳት ዝግጁ ነኝ አለች

የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ዬኦቺኦል ዩን   ለዴሊ ኒውስ (Daily News) እንደገለጹት ግብፅ በአባይ ግድብ ዙሪያ የምታደርገው ድርድር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ በመሆኑ ያለባትን የውኃ ችግር አሁንም ከፍተኛ በመሆኑ ይህን ለመቅረፍ ከጎኗ ሆና እንደምትረዳ ገልፀዋል።    በግብፅየኮሪያ   አምባሳደር ዬኦቺኦል ዩን   የኮሪያ ካምፓኒዎች በውኃ እጥረት ዙሪያ ያለባትን ችግር በሌላ አማራጭ መቅረፍ እንደሚቻል ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ኮሪያ ዝግጁ ነች ብለዋል።   የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ ኦክቶበር 13 ቀን ባደረጉት ንግግር ያለባትን የውኃ ችግር ለመቅረፍ ሌላ አማራጭ እንጠቀማለን ማለታቸው አይዘነጋም ። ፕሬዝዳንቱ   ባህሮችንና በሰሜን የሚገኙ ውቅያኖሶችን ተንተርሰው ነው ይህን ለማለት የቻሉት።     የኮሪያ ካምፓኒዎች በኢንቨስትምንት በኩል በግብፅ ለመሳተፍና ይበልጥ ንግዳቸውን ለማስፋት ፍላጎት ያላቸው መሆኑንም አምባሳደሩ ገልፀዋል።ይህም የታክስ ሁኔታንም ይጨምራል ብለዋል።   የሀገሪቱ የፋይናንስ የኢንቨስትመንት ሚኒስቴር መሥሪያቤትና   የኢንተርናሽናል ኮርፕሬሽን ከኢምባሲው ጋር በደንብ ተቀራርበው በመሥራት ይገኛሉ ብለዋል።     ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኮሪያ ካምፓኒዎችን ገንዘባቸውንና ንዋያቸውን በግብፅ እንዲያውሉ እየረዳቸው ይገኛል ብሏል።   ከፍተኛ የኮሪያ የቢዝነስ የልዑካን ቡድን   እ.ኤ.አ በ2019 ከኦክቶበር 8-10 ድረስ ግብፅን ጎብኝተዋል።    ኮሪያ ወደ ግብፅ እ.ኤ.አ በ2019 ላለፉት ስምንት ወራት ኤክስፖርት ያደረጉት 1.133 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው።ኮሪያ ከግብፅ ኢምፖርት ያደረገችው ደግሞ 102 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው።   ይህም   እ.ኤ.አ በ2018 ጋር ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ኮሪያ ኤክስፖርት ያ

ብሄርና ዘረኝነት የነገሰባት ሀገር

Image
ወያኔ/ኢህአዲግ   የአቀጣጠለው የዘረኝነት ተክል ዛሬ አብቅሎ በየአካባቢው ለበርካታ ሰዎች ከየቦታው መፈናቀልና መሰደድ እንዲሁም መሞት ምክንያት እየሆነ ነው።   በቅርቡ ጁሀር መሐመድ በፌስ ቡኩ ላይ የለጠፈውን ተንተርሶ ግሎባል Global Voices እና ሌሎች የሚዲያ ወገኖች በትንሹ ለ86 ሰዎች መሞት ምክንያት ስለ ሆነው የዘረኝነት ተግባር በተመለከተ   እንደሚከተለው አጠናቅረነዋል።     ጁሀር መሐመድ ከ18ሺህ በላይ ላይክ ባሉለትና ከ5.1ሺህ በላይ አስተያየት በሰጡበት 7.7 ሺህ ሼር የተደረገበትና ኦክቶበር 23 ቀን 2019 እ.ኤ.አ 05:09 በፌስ ቡክ ላይ የለጠፈው እንዲህ   ይነበባል ። «ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ ፦በመኖሪያዬ አካባቢ በቁጥር በርካታ ታጣቂ እየተሰማራ እንደኾነ እያስተዋልን ነው።ይህ የታጠቀ ኃይል ከሕግ አግባብ ውጪ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ተቆጥቦ ወደ ኋላ እንዲመለስ በአጽንኦት እንጠይቃለን ።ማንኛውም ታጥቆ በዚህ ጭለማ ወደ መኖሪያ ግቢያችን ለጥቃት የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ኾነ ቡድን ላይ የጥበቃ አካሉ ሕጋዊ መብቱን ተጠቅሞ የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል ።ይኽን ከሕግ አግባብ ውጪ የሚደረግን እንቅስቃሴ ለመከላከል በሚደርሰው ግጭት እና ጉዳት ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደው ያለምንም ተጨባጭ ምክንያትና ማሳሰቢያ ኃይል ያሰማራው አካል መሆኑን ሕዝቡ እንዲያውቅልን እንጠይቃለን» ይላል።   ይህ በሶሻል ሚዲያ ላይ የተሰነዘረው የጁሀር መልዕክት በበርካታ ዩንቨርስቲዎች ጭምር ተቀስቅሶ ፖለቲከኞች ፤የኅይማኖት አባቶች፣ሕፃናቶችና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ለሞት ተዳርገዋል።በኖቭምበር 2019   እ.ኤ.አ በወልዲያ ሁለት የኦሮሞ ተማሪዎች ሞተዋል።ትግስት ጌሜ በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ እንዲህ በማለት በትዊተር ገጿ ላይ ትገልጸዋለች