በኢትዮጵያ- ውያኔ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቀ
በዶክተር አብይ የሚመራው አዲሱ የኢህአዲግ የብልጽግና ፓርቲን የሚቃወመው የትግራዩ ፓርቲ ወያኔ የኦዲፓ፣የአዲፓ እና የደቡብ ሕዝቦች ዲሞክራሲ ፓርቲ ያቋቋሙት የብልጽግና ፓርቲ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በዶክተር ደብረፅዮንና በአቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ይፋ አድርጓል። በተለይም ዶክተር አብይ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ቡርቱካንን የሾሞት ለዚሁ ማስፈፀሚያ እንደሆነና ገና አዲሱ የብልጽግና ፓርቲያቸው እውቅና በምርጫ ቦርድ ሳይሰጠው ከሕገ መንግስቱ እውቅና ውጭ ፓርቲውን ይፋ ማድረጋቸው ሕገወጥ ተግባር መሆኑን የሕወአት አመራሮቹ ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው እንደሚሉት ሌላው ቀርቶ ሀገሪቷ ሰላምና መረጋጋት በለሌበት ሁኔታ ምርጫው እንዲካሄድ መደረጉ ተገቢ ካልሆነም ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቱን ሳላም ሳያደርጉ ዳግመኛ ቶሎ ብሎ ፓርቲ አቋቁመው ወደ ስልጣን መምበሩ በማናለብኝነት ለመቆናጠጥ ያላቸው ፍላጎታቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል። አቶ ጌታቸው ለድምፀ ወያኔ ቴሌቪዥን እንደገለፁት ፓርቲያቸው በርካታ ሰተቶች ቢኖርበትም በርካታ ስራዎች መስራቱን ገልፀው የአሁኑ መንግስት ግን ከሥራ ይልቅ የሕዝቡን ችግርና ብሶት ከመፍታት ይልቅ ወሬና አሉባልታ ላይ በማተኮር በማናለብኝነት ላይ ያተኮረ በመሆነ ሀገሪቱን የሚያስተዳድር ከሁሉም ፓርቲዎች ውጭ የሆነ ገለልተኛ የሆነ የሸምጋይ ወይንም የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ ቅድሚያ ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ተሰጥቶ ይህ ከተከናወነ በኋላ ወደ ምርጫው እንዲገባ አሳስበዋል። አለዛ ግን ሀገራችን ወደ ባሰ ትርምስና ብጥብጥ ልትገባ እንደምትችል ፍራቻቸውን ከወዲሁ ሳይገልፁ አላለፉም።