«ጋዜጠኝነትን ስትሰራ የጋዜጠኝነትን ኮፍያ ታረጋለ፤ አክቲቪስትም ስትሆን እንደዛው፤ ፖለቲከኛ ስትሆን የፖለቲካ ኮፍያ ታደርጋለ ዋናው የምትሰራውን ማወቅ ላይ ነው» ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
ጋዜጠኝ፣ አክትቪስትና ፖለቲከኛ እስክንድር ነጋ አንዳንድ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የአዲስ አበባ ባላደራ ኮሚቴን ማቋቋሙን አስመልክቶ እየተሰነዘረበት ያለውን ትችት እንደማይቀበለው ገለጸ። እስክንድር በፕሬሱ ላይ ከፍተኛ መስዋትነት ከከፈሉት ጋዜጠኞች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከስር ከተፈታ በኋላም «ኢትዮጲስ» ጋዜጣን በማሳተምና በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። ጋዜጣው ዘወትር ቅዳሜ በየሳምንቱ ስትወጣ በርካታ ውጣውረዶችን አይታ ነው ለአንባቢው የምትበቃው። በሌላ በኩል እስክንድር አክቲቪስትም ነው ከዚህ ሌላ የአዲስ አበባ ባላደራ ኮሚቴን በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ለእስክንድር ብዙ ሰዎች አንተ ከምትታወቅበት የጋዜጠኝነት ሙያ ባሻገር ፖለቲካና አክቲቪስት መሆንህን በብርቱ ይቃወማሉ ለዚህ ያለክ አስተያየት ምንድን ነው አልኩት ? እስክንድርም «ይሄ በጣም ደስ የሚል ጥያቄ ነው ፤ለእኔ ሁሉንም በአግባቡ መምራት ትችላለ ባይ ነኝ ። ጋዜጠኝነትን ሙያ ስትሰራ የጋዜጠኝነትን ኮፍያ ታረጋለ፤ አክቲቪስት ስትሆን እንደዛው ፤ፖለቲካን ስትሰራ የፖለቲካ ኮፍያ ታደርጋለ ዋናው ቁምነገር የምትሰራውን ስራ ማወቅ ላይ ነው » ይላል። «ጋዜጠኝነቱን ስትሰራ ከማንም ፖለቲካ ሳትወግን የራስህንም የፖለቲካ አመለካከት ሳታራምድ ሚዛናዊ ሆነ ትክክለኛውን ነገር መሥራት ነው። አክቲቪስትም ስትሆን እንደዛው ፖለቲከኛም ስትሆን መስራት ያለብህን ነገር መስራት ነው »በማለት ይገልጻል። እንደ እስክንድር በርካታ ተዋቂ የእንግሊዝም ሆነ የሌሎች ሀገር ጋዜጠኞች የራሳቸውን ፖለቲካ እያራመዱና እየተንቀሳቀሱ በአንፃሩ ዋንኛውን የጋዜጠኝነት ሙያቸውን እየሰሩ ይገኛሉ በማለት ከገለጸ በኋላ የእሱም ሁኔታ በአሁኑ ወቅት ከዚሁ ያልተለየ መሆኑን ይጠቁማል