የሰው ልጆችን ነፃነት (humans freedom )ምንድን ነው?
ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ ) በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ነፃነት ያስፈልጋቸዋል። የመናገር ወይንም ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት ፤ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በሰላም የመንቀሳቀስ ወይንም በሰላም ወጥቶ በሰለም የመግባት ነፃነት፤የዲሞክራሲ ነፃነት፤የፖለቲካ ነፃነት ፣የማህበረሰብ ነፃነት ፤የኢኮኖሚ ነፃነት፤የፍቅር ነፃነት፤የጓደኝነት ነፃነት ወዘተ. አሉ። በዓለማችን ያሉ ታላላቅ የፍልስፍና ሰዎች ነፃነትን (freedom ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፋፍሉታል። በአንደኝነት የነፃነት አሳብ ብለው የሚያስቀምጡት ሰዎች በእርስ በርስ ግንኙነታቸው ወቅት በአሳባቸው ውስጥ የፀነሱትን የነፃነት (freedom ) ከማህበረሰቡና ከመንግሥት አስተሳሰብ ጋር ባልተቃረነ መልኩ አብረው የሚኖሩትን ሕይወት ይመለከታል። በማለት ይገልጻሉ። ሁለተኛው ደግሞ ከመጀመሪያው ፍፁም የተለየ የሆነው የነፃነት እሳቤ ደግሞ የሰው ልጅ በዕለት ተዕለት ድርጊቱ የሚፈፅመውን ድርጊት የሚወስንበት የራሱ የሆነ ውስጣዊ የሆነ ነፃነት አለው በማለት ይገልጻሉ።በሌላ አነጋገር ይህን «ስነልቦናዊ ነፃነት»(psychological freedom )በማለት ይጠሩታል። ሦስተኛውና የመጨረሻው የሰው ልጅ በውስጡ ከሚነሱት ግጭቶች (conflict) ነፃ የሚሆኑበትና ተፈጥሮውን ወደ ፍፁምነት በማድረስ ሊሆን የሚገባውን የነፃነት ሀሳብ የሚንሸራሸርበትና የሚጨብጥበት አንዱ የነፃነት አካል ነው። በማለት ይጠቁማሉ። በእርግጥ አንዳንድ ፈላስፎችና የስነመለኮት ምሁራኖች የሰው